BBC News, አማርኛ - ዜና

እንዳያመልጥዎ

አነጋጋሪ ጉዳይ

ከየፈርጁ

አጃኢብ!

የተመለሱ ጥያቄዎች

  • ሰው ሠራሽ አስተውሎት

    የሰው ሠራሽ አስተውሎት ምጡቅነት ከሰው ልጆች ቢበልጥ ምን ይፈጠራል?

    በቴክኖሎጂ ዕድገት ታዋቂ ከሆኑ ንድፈ ሐሳቦች አንዱ ‘The technological singularity’ ወይም ‘The singularity’ ነው።‘ዘ ሲንጉላሪቲ’ ንድፈ ሐሳባዊ የወደፊት ነጥብ ነው። ያ ነጥብ ቴክኖሎጂ ከቁጥጥር የሚወጣበትና መቀልበስ የማይቻል እንደሆነ ንድፈ ሐሳቡ ያስቀምጣል።የሰው ልጆች በራሳቸው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፈጠራ ተበልጠው የሰው ልጅ ሥልጣኔ ጥያቄ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል?

  • የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት

    ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑ የታወጀው ኤምፖክስ ክትባት አለው?

    የዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑ የታወጀው የኤምፖክስ (ዝንጀሮ ፈንጣጣ) አዲሱ ዓይነት ዝርያ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። ከዚህ በፊት ካጋጠሙት ሁሉ የበለጠ አደገኛ መሆኑ የተነገረለት ይህ ዝርያ ወደ መካከለኛው እና ምሥራቅ አፍሪካ እየተዛመተ ይገኛል።

  • የተቀጠለ የዓይን ሽፋሽፍት ያላት ሴት

    አደገኛ ጉዳትን የሚያስከትለው የሴቶች የዐይን ሽፋሽፍት መቀጠል

    ሽፋሽፍት በተፈጥሯዊ ይዞታው ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። በዐይን በኩል የሚገባ አደገኛ ባክቴሪያዎች እና ቫይረሶችን ይከላከላል። ነገር ግን ሽፋሽፍትን ለማስረዘም የሚውሉ ቁሶች እና ማጣበቂያዎች ለዐይን ጤና ጠንቅ የመሆን ሰፊ ዕድል አላቸው። የዐይን ሽፋሽፍትን በማስረዘም ሂደት ምን ችግር ሊያጋጥመን ይችላል?

  • ስለአዲሶቹ ኮቪድ ዝርያዎች ምን ይታወቃል?

    አዳዲሶቹ ፍለርት የኮቪድ-19 ዝርያዎች ምን ያህል አሳሳቢ ናቸው?

    ከጥቂት ዓመታት በፊት መላውን ዓለም አዳርሶ ሚሊዮኖችን በመያዝ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለሞት የዳረገው ኮቪድ 19 ጉዳቱ ቢቀንስም አሁንም የሰው ልጅ የጤና ስጋት መሆኑ አላበቃም። ይህ በትንፋሽ የሚተላለፈው ቫይረስ ባለፉት ዓመታት ዝርያውን እና የጉዳት አቅሙን እየቀያየረ ይገኛል። አሁን ደግሞ የቫይረሱ አዲስ አይነት ዝርያ መገኘቱ እየተነገረ ነው። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ ፍሊርት (FliRT) የሚል ስም የተሰጣቸው አዲስ ዝርያዎች በዓለም ላይ በጣም ዋናዎቹ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ሆነዋል። በዚህ ዙሪያ ማወቅ የሚገባዎትን መረጃ አጠናቅረናል።

  • ቁመቷን ርዝመት ለመጨመር ቀዶ ህክምና ያደረገችው እሌይን ፋኦ

    ቁመትን በቀዶ ህክምና በ8 ሴንቲ ሜትር ለማስረዘም የተከፈለ ከባድ መስዋዕትነት

    አጭር ቁመቷን ሁልጊዜም ትጠላው ኤሌይን ዋናው ትኩረቷ ቁመቷ ነበር። ረዥም መሆን ማለት የተሻለ፣ የበለጠ ቆንጆ ነው ብላ ታስብ ነበር። ረዣዥም ሰዎች በሕይወት ላይ የበለጠ ዕድል እንደሚከፈትላቸው ይሰማት እንደነበር ትናገራለች። እናም ቁመቷን በቀዶ ህክምና ለማስረዘም ያለፈችበት ቀዶ ህክምና ጤናዋን እና ሕይወቷን አመሳቅሎታል።

  • የምርመራ ውጤት

    በአፍሪካ የጤና ስጋት መሆኑ የታወጀው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? እንዴትስ ይተላለፋል?

    ኡጋንዳ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አስታውቃለች። ሌሎቹ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ከኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ብሩንዲ ውስጥም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።ለመሆኑ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ በፍጥነት እየተስፋፋ ያለው ለምንድን ነው?

  • ቶሞ በአቅራቢያው ባሉ የሰውነት እንቅስቃሴ የሚከታተሉ ካሜራዎች ፊት በፍጥነት ይሮጣል።

    በኦሊምፒክ ወርቅ ሊያመጡ የሚችሉ ስፖርተኞችን የሚተነብየው ቴክኖሎጂ

    የኦሊምፒክ ወዳጆችን አዲስ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚሠራ ቴክኖሎጂ ትኩረታቸውን ስቦታል። ቴክኖሎጂው ለወደፊት በኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ሊያገኙ የሚችሉ ሰዎችን መለየት የሚያስችል ነው። የዚህ ፈጠራ ባለቤቶች ዓላማቸው የላቀ የስፖርት ሳይንስን በሁሉም የዓለም ጥጎች ማዳረስ ነው።

  • የኢትዮጵያ ፓስፖርት

    የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋጋ ከሌሎች አገራት ጋር እንዴት ይነጻጸራል?

    የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋጋ ከሌሎች አገራት ጋር እንዴት ይነጻጸራል?

  • ጡት የሚጠባ ሕጻን

    ለሕጻናት በጣም አስፈላጊ በሆነው ጡት ማጥባት ዙሪያ ያሉ 7 የተዛቡ አመለካከቶች

    የነሐሴ የመጀመሪያው ሳምንት የዓለም ጡት የማጥባት ሳምንት ነው። የዘንድሮው መሪ ቃል ትኩረቱ የሚያጠቡን እናቶችን በመደገፍ ላይ ያተኮረ ነው። የተለያዩ ጡት ስለማጥባት የሚነገሩ የተዛቡ አመለካከቶች ሴቶች ላይ ጫና ያሳድራሉ። ከእነዚህ የተዛቡት አመለካከቶች መካከል የተወሰኑትን እንመለከታለን። እናንተ የምታውቋቸው ስለጡት ማጥባት የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ?

  • ዳንሰኛ

    ‘ብሬክዳንስ’ እንዴት በኦሊምፒክ መድረክ የውድድር ስፖርት ሆኖ መጣ?

    አትሌቶችን በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች በማሳተፍ የሚታወቀው ኦሊምፒክ አሁን ደግሞ ዳንሰኞችን ማሳተፍ ጀምሯል። “ብሬክዳንስ” በፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አንድ የመወዳደሪያ ዘርፍ ሆኖ ቀርቧል። እአአ በ2018 በቦነስ አይረስ በተካሄደው የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ብሬክዳንስ ተካቶ ነበር። ለመሆኑ የዚህ ዳንስ አመጣጥ ምን ይመስላል?

  • ብር

    ገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ምንድነው? ጥቅም እና ጉዳቶቹስ?

    አንድ አገር መገበያያ ገንዘብ ከዋና ዋና የውጭ አገራት ገንዘቦች በተለይም ከአሜሪካን ዶላር አንጻር የነበረው ዋጋ ሲቀንስ የመግዛት አቅሙ ቀንሷል ይባላል። ለምሳሌ ያህል አንድ ዶላር ይመነዘርበት ከነበረበት 57 ብር ወደ በ76 ብር መመንዘር ከጀመረ የብር መግዛት አቅም ተዳክሟል ይባላል። በርካታ አገራት ፍላጎት እና አቅርቦትን ለመቆጣጠር የመገበያያ ገንዘባቸውን ያዳክማሉ።

  • የሄፒታይትስ ቫይረስ

    ራሳችንን የጉበት በሽታ ከሆነው ሄፒታይትስ እንዴት መከላከል እንችላለን?

    በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሄፒታይትስ በሽታ እንዳለባቸው ስለማያውቁ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የጤና ኃላፊዎች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ሐምሌ 21 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሄፒታይትስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልዕክት ነው። ሄፒታይትስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ሰዎች ሞት ምክንያት ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ቁጥሩ እየጨመረ መጥቷል። በሽታው መከላከያ፣ ክትባት እና ሕክምና አለው?

ሌላ ዕይታ

ብዙ የተነበቡ