Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩቶ ተመረጡ


ሩቶ ተመረጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:30 0:00

ሩቶ ተመረጡ

በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ የተሣተፉ ዕጩዎች ሁሉ ውጤቱን ለመቀበል ለገቡት ቁርጠኛነት ተገዥ ሆነው እንዲቀጥሉ የተበበሩት መንግሥታት ድርጅት አሳሰበ።

ኬንያዊያን ባለፈው ሣምንት በሰጡት ድምፅ የአሁኑን ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶን ለፕሬዚዳንት መምረጣቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ አስታውቋል።

ናይሮቢ ላይ የተካሄደው ረብሻ የታየበት ውጤት የማሳወቂያ ሥነ-ሥርዓት ለሰዓታት ዘግይቶ ሲጀመር ፀጥታ አስከባሪዎች ሲያውኩ የነበሩ ሰዎችን እየገፈተሩ ሲያስወጡ በቀጥታ ሥርጭት ተላልፏል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ 7.18 ሚሊዮን ድምፅ ወይም 50.49 ከመቶ፣ ተፎካካሪያቸው ራይላ ኦዲንጋ 6.4 ሚሊዮን ድምፅ ወይም ከመራጩ የ48.85 ከመቶውን ድጋፍ ማግኘታቸውን የኮሚሽኑ ሃላፊ ዋፉላ ቼቡካቲ ባሰሙት እወጃ አስታውቀዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች በዛሬ ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ሁሉም ወገኖች የህግ መፍትኄ ብቻ እንዲፈልጉ አሳስበው “ለምርጫው ሂደት ሰላማዊ ፍፃሜ የህግ የበላይነት መከበር ቁልፉ መንገድ ነው” ሲሉ አሳስበዋል።

ዝርዝሩን እንግዱ ወልዴ ያቀርበዋል።

XS
SM
MD
LG