Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ 55 ሚሊየን ሰዎች የረሀብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል


ማዕከላዊ አፍሪካ 2016
ማዕከላዊ አፍሪካ 2016

ከጊዜ ወደጊዜ እየናረ የሚሄደው የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ባሉ ሀገራት 55 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች እራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እማይችሉበት ትግል ውስጥ እንደከተታቸው የመንግስታቱ ድርጅት የረድኤት ተቋማት ትላንት አርብ አስታውቀዋል።

ባለፈው አምስት ዓመት ውስጥ ከሰኔ እስከ ነሃሴ ባሉት ወራት ረሃብ የሚያጋጥማቸው ዜጎች አሃዝ በአራት እጥፍ ማደጉን ፣ እንዲሁም የጥምር ዲጂት የምጣኔ ሃብት ማዘቅዘቅ፣ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ባለበት መቆሙ እና እየተደጋገሙ የሚነሱ ግጭቶች ቀውሱን ማባባሳቸውን ተገልጿል።

በአደጋው ከተጎዱት ሀገራት መካከል ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ሴራሊዮንና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ከ2600 በላይ ሰዎች በአስከፊ ረሃብ ውስጥ የሚገኙባት ማሊ ተጠቃሾች መሆናቸውን የአለም የምግብ መርሃግብር፣ የመንግስታቱ ድርጅት የህጻናት ፈንድ ዩኒሴፍ እና የምግብ እና የግብርና ተቋም የጋራ መግለጫ አስታውቋል። በምዕራብ አፍሪካ የአለም የምግብ መርሃግብር ጊዜያዊ ዳይሬክተር ማርጎ ቫንደርቨልደን “ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን እርምጃ ለመውሰድ ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል።

ተቋማቱ ባለው የምግብ እጥረት የተነሳ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጨመሩንም አስታወቀዋል። 16.7 ሚሊየን የሚሆኑ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት ያነሱ በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ያሉ ህጻናት በጽኑ የተመጣጠን ምግብ እጥረት ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል።

በክልሉ ከውጭ በሚገቡት የምግብ ምርቶች ላይ ያለው ጥገኝነት በተለይ እንደ ጋና፣ ናይጄሪያ እና ሴራሊዮን ያሉ ከፍተኛ የዋጋ ንረትን በሚዋጉ ሀገራት ላይ ጫናውን አጠንክሮታል።

በምዕራብ አፍሪካ የአለም የምግብ እና የግብርና ድርጅት ፋኦ ክልላዊ አስተባባሪ ሮበርት ጉዪ “ለተከሰተው ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምላሽ ለመስጠት የሀገር ውስጥ የምግብ ምርትን የሚያሳድጉ እና የሚያበዙ ፖሊሲዎች መተዋወቅ አለባቸው ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG