Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን፣ ኦባማና ክሊንተን በሚገኙበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 25 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል


የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጆን ኤፍ ኬኔዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ኒው ዮርክ እአአ መጋቢት 28/2024
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጆን ኤፍ ኬኔዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ኒው ዮርክ እአአ መጋቢት 28/2024

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ቢል ክሊንተን በሚገኙበት፣ ዛሬ ምሽት በኒው ዮርክ ከተማ በሚካሄደው የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የምርጫ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ 25 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ዘመቻው አስታውቋል። የገንዘብ መጠኑ ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ከፍተኛ የምርጫ ገንዘብ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

ይህ ከፍተኛ የገንዘብ መዋጮ፣ ከህዝብ በተሰበሰበ ድምፅ ዝቅተኛ ድጋፍ ያገኙት ባይደን ከዲሞክራቲክ ፓርቲያቸው የተቸራቸውን ትልቅ ድጋፍ የሚይሳይ መሆኑም ተገልጿል። ገንዘቡንም፣ እ.አ.አ በ2016 ዲሞክራቷን ሂላሪ ክሊንተንን አሸንፈው የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ለመያዝ ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰብ እንደማያስፈልጋቸው ካስመሰከሩት እና የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት ዶላንድ ትራምፕ ጋር ለሚኖራቸው ፍልሚያ ይጠቀሙበታል።

የዴሞክራቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ከሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የተሻለ የምርጫ ገንዘብ ማሰባሰብ የቻሉ ሲሆን፣ እስከየካቲት መጨረሻ በነበረው ጊዜ አራት እጥፍ የሚበልጥ ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው እንዳለ ተመዝግቧል፡፡

ባይደን እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ 155 ሚሊዮን ዶላር ሲኖራቸው ትረምፕ የነበራቸው 37 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ኒዮርክ ውስጥ በራዲዮ ሲቲ የሙዚቃ አዳራሽ የሚካሄደው ዝግጅት ስቲቨን ኮልቤር በተባለ እውቅ የምሽት አዝናኝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ አወያይነት፣ ከባይደን፣ ኦባማ እና ክሊንተን ጋር የሚደረግ ውይይት ይገኝበታል፡፡

ኩዊን ላቲፋ፣ ሊዞ፣ ቤን ፕላት፣ ሲንቲያ ሪቮ እና ሊያ ማይክል የመሳሰሉ ድምጻዊያንና ሙዚቀኞችም ዝግጅቶቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ ደጋፊዎች በዛሬው ዝግጅት ለመሳተፍ ከገቢው ማሰበሳቢያው ሳምንት ቀደም ብለው የገንዘብ ድጋፋቸውን ሲሰጡ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዛሬው ምሽት ዝግጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዝቅተኛው የመግቢያ ዋጋ 225 ዶላር ነው፡፡ በምሽቱ ከለጋሾች በርካታ ገንዘብ ይገኛል ተብሎ ሲጠበቅ ከሶስቱ ፕሬዚዳንቶች ጋር ፎቶግራፍ ለመነሳት 100ሺ ዶላር ያስከፍላል፡፡

250ሺ ዶላር አንደኛው የራት ግብዣ ላይ የሚያሳትፍ ሲሆን 500ሺ ዶላር ከምሽቱ ልዩ የክብር እንግዶች ጋር በቅርበት ያገናኛል፡፡

የገንዘብ ማሰባሰቢያው ከትረምፕ አንጻር የባይደንን የገንዘብ አቅም ይበልጥ የሚያሳድግ ሲሆን የዝግጅቱ ስኬት ለባይደን እና ለምክትል ፕሬዝዳንት ከማላ ኻሪስ ያለውን ጠንካራ ድጋፍ ያሳያል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG