Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሠላሳ ዓመታት ያለፉት የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ


ሠላሳ ዓመታት ያለፉት የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:09 0:00

ሠላሳ ዓመታት ያለፉት የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ

በኢትዮጵያ ሥነ ሕዝብን በአግባቡ ማስተዳደር ባለመቻሉ፥ ሥራ ዐጥነትን፣ የኑሮ ውድነትንና ስደትን ጨምሮ ለተለያዩ አገራዊ ቀውሶች ምክንያት እየሆነ ነው፤ ሲሉ የዘርፉ ባለሞያዎች ገለጹ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የሥነ ሕዝብ እና አካባቢ ጥናት ተመራማሪው ፕሮፌሰር አማረ ሰውነት፣ ከ30 ዓመታት በላይ የሆነው የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ፣ አሁን ያሉትን ችግሮች ለይቶ ሊፈታ በሚችል መልኩ ማሻሻል እንደሚገባ ያመለክታሉ፡፡

የአገሪቱ ፖለቲካዊ ኹኔታ “የሥነ ሕዝብ ጉዳይ እንዲረሳ አድርጎታል፤” የሚሉት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የሥነ ሕዝብ ባለሞያ አቶ አወቀ አጉማስ በበኩላቸው፣ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መሠረት መካሔድ ከነበረበት ጊዜ ሰባት ዓመታት ማለፋቸውን በማሳያነት ያነሣሉ፡፡ ይህም አገሪቱን ብዙ ዋጋ እያስከፈላት ነው፤ ሲሉ ይስረዳሉ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በበኩሉ፣ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራን ለማካሔድ በስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራሙ አማካይነት ዕቅድ መያዙን፣ መንግሥታዊ ብዙኀን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡

መንግሥት ቆጠራውን እንደሚያካሒድ በተለያዩ ጊዜያት ቢገልጽም፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት በተደጋጋሚ ሲያራዝም መቆየቱ ይታወቃል፡፡ አሁን ግን የአማራ ክልልን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች የሰላሙ ኹኔታ እየተሻሻለ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጾ፣ ለሕዝብ እና ቤት ቆጠራው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸውን ጠቁሟል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG