Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማኅበራዊ ትስስር ገጾች- ሐሰተኛ የጤና መልእክቶች እና ችግሮቻቸው


የማኅበራዊ ትስስር ገጾች- ሐሰተኛ የጤና መልእክቶች እና ችግሮቻቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:10 0:00

የማኅበራዊ ትስስር ገጾች- ሐሰተኛ የጤና መልእክቶች እና ችግሮቻቸው

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ አማራጮች ሐሰተኛ የጤና መልእክቶች እየተሰራጩ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር ባለሥልጣንና ሁለት የሕክምና ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡
ሚኒስቴሩ ባለፈው መስከረም ወር አውጥቶት በነበረው መግለጫ፣ በተለይም በቲክ ቶክ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ፣ የኅብረተሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ሐሰተኛ የጤና መልእክቶች በብዛት በመሰራጨት ላይ እንደሚገኙ ጠቁሟል፡፡ ድርጊቱ፥ የጤና ሞያተኛ ሳይኾኑ የጤና ሞያዊ ምክር እንሰጣለን በሚሉ ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች እንደሚሰራጭም አስታውቋል፡፡
ተጠቃሚዎች፣ የጤና መረጃዎችን ከትክክለኛ የመረጃ ምንጭ እና ከጤና ባለሞያ ብቻ ማግኘት እንደሚገባቸው ተገንዝበው፣ በማኅበራዊ የትስስር ገጽ አማራጮች ከሚሰራጩ ሐሰተኛ የጤና መረጃዎች እና ከሚያስከትሏቸው የጤና አደጋዎች እንዲጠበቁ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል፡፡
የሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያ ከወጣ ጥቂት ወራት ቢቆጠሩም ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ መኾኑን፣ የጤና ባለሥልጣናት እና የሕክምና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ በሚኒስቴሩ የጤና የማኅበራዊ ሚዲያ አስተዳደር እና የኮምዩኒኬሽን ቡድን መሪ ዶ/ር ዳንኤል በትረ፣ በማኅበራዊ የትስስር ገጽ አማራጮች ላይ የሕክምና ትምህርት የሚሰጡት ዶ/ር ሰይፈ ወርቁ እና በአለርት ሆስፒታል ሐኪም እና “ጤና ሰብ” የሚባለው የማኅበራዊ ሚዲያ መምህር ዶ/ር ዝማሬ ታደሰ፣ ሐሰተኛ የጤና መልእክቶች በብዛት በመሰራጨት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ሐሰተኛ መረጃዎቹን የሚያሰራጩት የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ባለቤቶች፣ ስማችንንና ምስሎቻንን አላግባብ እየተጠቀሙ ምክር እንሰጣለን በሚል ገንዘብ ይቀበላሉ፤” ሲሉም ባለሞያዎቹ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG