Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሂዝቦላ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወነጨፈ


የእስራኤል የአየር ጥቃት ባደረሰው ጉዳት የአካባቢው ሰዎች ፍርስራሽ አካባቢ ተሰባስበው ደቡብ ሊባኖስ፣ በሄባሪዬ መንደር፣ እአአ መጋቢት 27/2024
የእስራኤል የአየር ጥቃት ባደረሰው ጉዳት የአካባቢው ሰዎች ፍርስራሽ አካባቢ ተሰባስበው ደቡብ ሊባኖስ፣ በሄባሪዬ መንደር፣ እአአ መጋቢት 27/2024

በሊባኖስ የሚገኘው ሂዝቦላ፣ 30 የሚሆኑ ሮኬቶችን ወደ ሰሜን እስራኤል አስወንጭፏል። ሊባኖስ ለጥቃቱ ኃላፊነት በመውሰድ፣ ሮኬቶቹን የተኮሰው እስራኤል ሰባት የሊባኖስ ሱኒ ሙስሊም አባላትን በአየር ጥቃት መግደሏን ተከትሎ መሆኑን አመልክቷል።

የሐማስ እና እስራኤል ጦርነት ከጀመረ ወዲህ፣ ሂዝቦላ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን ሲያስወነጭፍ ቆይቷል። በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር መካከል በየቀኑ ሁከት የሚታይ ሲሆን፣ ሂዝቦላ እና እስራኤል ወደለየለት ጦርነት እንዳይገቡ ዓለም አቀፍ ሸምጋዮች ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

የተኩስ አቁም ላይ ለመድረስ ሐማስ ያቀረባቸውን እና “ቅዠት” ብለው የገለጹትን ቅድመ ሁኔታን እንደማይቀበሉ፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ትላንት ማክሰኞ አስታውቀዋል።

እስራኤል ጦርነቱን እንድታቆምና ከጋዛ ሙሉ ለሙሉ እንድትወጣ ሲል ሐማስ የሚያቀርበውን ጥያቄ አትቀበልም። በመሆኑም፣ ሐማስ በቅርቡ የቀረበውን የተኩስ ማቆም ሃሳብ ውድቅ አድርጓል።

እስራኤል ሐማስን ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ እንደምትሻ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር በቅርቡ እንዳስታወቀው፣ በጦርነቱ እስከ አሁን 32 ሺሕ ሰዎች ሲገደሉ፣ 74 ሺሕ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG