Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የሰሜን ኮሪያን ማዕቀብ ክትትል የሚያስቀጥለውን ውሳኔ ድምጽን በመሻር ሥልጣኗ ጣለችው


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት

ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ክትትል እንዲቀጥል የቀረበውን ውሳኔ ድምጽን በድምጽ በመሻር ሥልጣኗ ዛሬ ሐሙስ ውድቅ አድርጋዋለች።

በዩናይትድ ስቴትስ የተደገፈው የፀጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ የክትትል ቡድኑን የቆይታ ጊዜ ለአንድ ዓመት የሚያራዝም ሲሆን ሩስያ ድምጽ የመሻር ውሳኔ ስራውን እንዲያቆም ያደርገዋል፡፡

ከ15ቱ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት 13ቱ ውሳኔውን ሲደግፉ ሩሲያ ተቃውማለች፡፡ ቻይና ድምጸ ተአቅቦ አድርጋለች፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ ከድምጽ መስጫው በፊት ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር ምዕራባውያን ሀገራት ሰሜን ኮሪያን "ለማነቅ" እየሞከሩ ነው፣ የተጣሉት ማዕቀቦች የኒው ክሊየር መርሐ ግብሯን ለመቆጣጠር ውጤታማ አለመሆናቸው እና ከእውነታው የራቁ መሆናቸው ታይቷል” ብለዋል፡፡

ውሳኔው ተግባራዊ ሆኖ የሚቀጥለውን ማዕቀብ እንደማይቀይረው የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG