Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ የኢትዮ-ሶማሊያን ውጥረት የሚያረግብ ቀጣናዊ የባሕር ውል እንዲዘጋጅ ጠየቀች


ኬንያ የኢትዮ-ሶማሊያን ውጥረት የሚያረግብ ቀጣናዊ የባሕር ውል እንዲዘጋጅ ጠየቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:52 0:00

ኬንያ የኢትዮ-ሶማሊያን ውጥረት የሚያረግብ ቀጣናዊ የባሕር ውል እንዲዘጋጅ ጠየቀች

ኢትዮጵያ፣ በራስ ገዟ ሶማሊላንድ በኩል የባሕር በር ለማግኘትና የባሕር ኀይል መደብ ለመመሥረት የምታደርገውን ጥረት ተከትሎ ከሶማሊያ ጋራ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ የሚያግዝ ቀጣናዊ የባሕር ውል እንዲዘጋጅ ኬኒያ መጠየቋን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣኗ ተናግረዋል። የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ፣ ትላንት ኀሙስ ከኬኒያው አቻቸው ጋራ በናይሮቢ ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ መክረዋል። የኬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ኮሪር ሲንጓይ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ዕቅዱን እየመረመሩት እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በባሕር ንግድ ስምምነት መሠረት በሚዘጋጀው ውል ከተስማሙ፣ ለኢትዮጵያ የባሕር በርን ያለምንም መስተጓጎል ለንግድ ዓላማ እንድትጠቀም ያግዛታል፤ ለሶማሊያ ደግሞ የግዛት ሉዓላዊነቷን የሚያረጋግጥ ይኾናል፤ ብለዋል።

ባለሥልጣኑ አክለውም፣ ቀጣናዊ የባሕር ውሉን የሚያዘጋጀው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት በምኅጻሩ ኢጋድ እንደሚኾንም አስታውቀዋል።

የሮይተርስን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG