Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግስታቱ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ17 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ መደበ


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ

በኢትዮጵያ እየተባባሰ ለመጣው የምግብ ዋስትና እጦት የ17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ አስታወቁ። አዲስ የተመደበው ይህ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያን ለተጨማሪ አደጋ ያጋለጠው ‘ኤልኒኞ’ የአየር መዛባት ያስከተለው ድርቅ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የከፋ ጉዳት ሊያስከትል መቻሉ ያሳደረውን ብርቱ ስጋት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያን የገጠመው የምግብ ዋስትና እጦት በመጭው ወራትም እየበረታ ሊሄድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ከሐምሌ እስከ መስከረም ባሉት የክረምት ወራት ውስጥ በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከዚህ ቀደም የተከሰተው ድርቅ እና በሃገሪቱ ያሉት ግጭቶች አሁንም ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ቀጥለዋል። በሌላ በኩል የጎርፍ መጥለቅለቅ ተጨማሪ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከ2013 እስከ 2015 ባለው ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ጨምሮ በሃገሪቱ በተከታታይ ለደረሱ ምስቅልቅል ሁኔታዎች የተጋለጡ ማሕበረሰቦችን ከገጠማቸው የከፋ ጉዳት ለመታደግ ያለው ዕድል አጭር ዕድሜ ዘላቂ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG