Svoboda | Graniru | BBC Russia | Golosameriki | Facebook

በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ፕሬዚደንት ከአሜሪካ የንግድ መሪዎች ጋራ ተወያዩ


ፎቶ ፋይል፦ የቻይና ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ
ፎቶ ፋይል፦ የቻይና ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ

የቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ የአሜሪካ የንግድ ማኅረሰብ መሪዎችን ቤጂንግ በሚገኘው ‘በታላቁ የሕዝብ አዳራሽ’ ተቀብለው አነጋግረዋል።

አዲሱን የአገሪቱ የንግድ ሕግ ተከትሎ መንግሥት ዓለም አቀፍ ባለሃብቶችን ለመሳብ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ተብሏል።

ቻይና አዳዲስ የሕግ ማነቆዎችን ማውጣቷን እና ርምጃዎችን መውሰዷን ተከትሎ፣ አገሪቱ በቀጥታ ከውጪ የምታገኘው ኢንቨስትመንት ባለፈው ዓመት ስምንት በመቶ ቀንሷል።

ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠታቸው፣ ሕጉን ልንጥሥ እንችላለን የሚለው ስጋት ባለሃብቶችን እንዲሸሹ አድርጓል። ያም ሆኖ ግን የቻይና ባልሥልጣናት የውጪ ባለሃብቶችን ለመሳብ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

አሜሪካውያን ባለሃብቶቹ ከሺ ጂንፒንግ ጋራ ለ90 ደቂቃ ያህል የተነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። ሺ ጂንፒንግ ባለፈው ኅዳር በአሜሪካ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት የእራት ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን፣ በሥፍራው ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG